asharaye.net
“እጆቼን ወደላይ አድርጋችሁ ቅበሩኝ”….ታላቁ እስክንድር – Mistre Aderaw
http://asharaye.net/2015/05/02/እጆቼን-ወደላይ-አድርጋችሁ-ቅበሩኝ-ታላቁ
8220;እጆቼን ወደላይ አድርጋችሁ ቅበሩኝ”….ታላቁ እስክንድር. May 2, 2015. አፈታሪክ ይሁን እውነታ አላውቅም ታላቁ እስክንድር እንዲህ አደረገ አሉ ወደ ሞት አፋፍ መቃረቡን ሲያውቅ ወዳጆቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው “ስትቀብሩኝ እጄን ወደላይ አርጋችሁ ቅበሩኝ” አለ ሰዎቹም ግራ ገብቷቸው ለምን እንደሆነ ጠየቁት እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው “እጄን ወደላይ አድርጋችሁ ቅበሩኝ ያልኩት ስሞት ምንም ነገር ይዤ እንዳልሄድኩኝ ሰዎች እንዲያዩ ነው ” አለ. ይህንን ያለው እንግዲህ በጊዜው አለምን ያስገበረው ታላቁ እስክንድር ነው በክንዱ ስንቱን ያስገበረው ታላቅ “ምንም ይዤ አልሄድም” ሲል ተናገረ. አንዳንዴ እራሴን እጠይቃለው የምንጨነቅለት ነገር ሁሉ ከዚህ አለም ስንሄድ ይዘነው የምንሄደው ካልሆነ ምንድን ነው ነጥቡ? ለምርጫ የምናቀርባቸው ነገሮች እራሱ የሞኝ ሰው ድርድር ነው. June 13, 2016.
asharaye.net
ምንጩን ትተን….ሌላ ጉድጓድ ቁፈራ – Mistre Aderaw
http://asharaye.net/2015/05/12/ምንጩን-ትተን-ሌላ-ጉድጓድ-ቁፈራ
ምንጩን ትተን….ሌላ ጉድጓድ ቁፈራ. May 12, 2015. ብዙዎቻችን በፍቅር ግንኙነታችንም ሆነ በተለያዩ ግንኙነቶቻችን ውስጥ ፍቅርን ያለቦታው እናስሰዋለን አለመፍለቅቂያው እንፈልገዋለን ለዚህም ነው ፍቅር ደብዛው የጠፋ የሚመስለው አንድ የውጪ ሃገር መምህር ይህንን ደስ በሚል ቋንቋ እንዲህ ገልጸውታል. 8220;በአህያው ጀርባ ላይ ሆነው አህያውን እንደመፈለግ ማለት ነው” ሲሉ ፍቅርን የምንፈልግ ሰውች ልክ አህያው ላይ ተቀምጦ አህያው ወዴት ነው ብሎ እንደሚፈልገው ሞኝ ማለት ነን በማንኛውም የህይወታችን ግንኙነት ውስጥ ፍቅር እንደጎደለን ካስብን ትክክለኛው መፍትሄ ልባችንን መመርመር ነው ለራሳችን ፍቅር ከሌለን ምንም እንኳን አለም ሁሉ ለኛ ፍቅር ቢኖረው ስሜቱን መረዳት አንችልም እናም ፍቅርን ፍለጋ በከንቱ እንዳክራለን. You Might Also Like. June 13, 2016. On የሚያሳስበን ችግ...
asharaye.net
አፈንጋጭ ሃሳቦች – Mistre Aderaw
http://asharaye.net/አፈንጋጭ-ሃሳቦች
አፈንጋጭ ሃሳቦች. በእለት ተእለት ኑሮዬ ውስጥ ድንገት ብልጭ ያሉብኝን ሃሳቦች የማሰፍርበት ገፅ ነው የኔን ብቻም ሳይሆን የሌሎች ፀሃፊያንን ሃሳብ አቀርብበታለው ከዘልማድ እይታ ውጪ የታዩ ምልከታዎችን ከለመድነው አስተሳሰብ ውጪ የታሰቡ ሃሳቦችን አስተላልፍበታለው አርዕስቱ እንደሚያስደረዳው አፈንጋጭ ሃሳቦች ከለመድነው አስተሳሰብ ያፈነገጡ ከሌላ አቅጣጫ የታዩ ሃሳቦች ማለት ነው. በዚህ አምድ ስር የሚሰፍሩ ፅሁፎችን ለማንበብ.ከተቻች ያለውን አፈንጋጭ ሃሳቦች የሚለውን በመጫን ወደፊት እና ወደኋላ በማድረግ ማንበብ ይቻላል. ምርትዎን ለመላው አለም በነፃ ያስተዋውቁ. ሶስት እርምጃ ለመክሊት; Three feet from your goal. 8220;አይን አይኑን የሚያዩት ውሃ ቶሎ አይፈላም”. ሎጎ ቴራፒ- ከትርጉም የለሽ እና ከተስፋ መቁረጥ ኑሮ የሚያላቅቅ የስነ-ልቦና ጥበብ (ክፍል ሁለት).
asharaye.net
Mistre – Mistre Aderaw
http://asharaye.net/author/mistre
8220;አይን አይኑን የሚያዩት ውሃ ቶሎ አይፈላም”. በሚስጥረ አደራው) አለም አንድ ሆናለች በሚባልበት በዚህ ዘመን ነገሮች እጅግ በፈጠኑበት በዚህ ጊዜ የፈለግነውን መረጃ በቀላሉ እና በአፋጣኝ በምናገኝበት ወቅት ነገሮችን በትዕግስት መጠበቁ እጅግ ከባድ ሆኖብናል የምንፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ በቀላሉ ማግኘት እንደምንችል የምንኖርበት ጊዜ እየሞገተን ነው ያለው ጥረት እና ትዕግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋቸው…. August 5, 2016. በሚስጥረ አደራው ለትክክለኛነት እና ለስህተተኛነት ጥያቄዎቻችንን መልስ እንደመስጠት ለእውነት እና ለሃሰት መለኪያችን መስፈርትን እንደማግኘት ለማንነታችን ትርጉምን እንደመፈልግ ህሊናን የሚረብሽ ምን ነገር አለ? ልብ እና አይምሮ ሲቃረኑ እምነት እና ፍላጎት ሲጣሉ ግለኝነትና ማህብረሰብ መስመር ሲለዩ ምን ማድረግ እንችላለን? July 30, 2016. July 11, 2016.
alelastudio.com
Alele Studio
http://www.alelastudio.com/index.html
Alela Magazine Current Issue. Alela Magzaine Volume 4 . Graphics . Graphics are pictures and movies created using computer aided tools. We do it from our hearts! Rendering . Rendering is the process of generating an image from a 2D or 3D model. We have years of experince! Animation . Animation is the process of making the illusion of motion for your. We do it at high stake! Magazine . Our publications are loved in DC, MaryLand and Virginia. DC Metro! ALELA Magazine Volume 1. ALELA Magazine Volume 2.
asharaye.net
“ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል?” አለኝ እግዜር – Mistre Aderaw
http://asharaye.net/2015/05/01/ሰዎች-እኔን-ማን-ይሉኛል-አለኝ-እግዜር
8220;ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል? 8221; አለኝ እግዜር. May 1, 2015. ከሁለት ሺህ አመታት በኋላ እግዜር ጥያቄውን ደገመው ሊያውም ለኔ……. የዛሬ ሁለት ሺህ አመት ገደማ ፈጣሪ በምድር በነበረበት ጊዜ ሃዋሪያዎቹን ሰብስቦ ” ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል? 8221; ሲል እንደጠየቃቸው አንብቤ ነበር ሃዋርያቱም ሰዎች አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎችም ኤሊያስ ሌሎችም ኤርሚያስ ወይም ከነብያት አንዱ ነው ብለው ያስባሉ እናዳሉት ምጽሃፉ ይናገራል. ዛሬ ከሁለት ሺህ አመታት በኋላ እግዜር ጥያቄውን ለዚህ ዘመን ሰዎች ደገመው እንዴት እኔን መረጠኝ? ትላንት ድንግት በሌሊት እግዜር ተገለጠልኝ አንድ ከባድ ጥያቄም ጠየቀኝ “የዚህ ዘመን ሰዎች ማን ይሉኛል? 8221; አለኝ ደነገጥኩኝ በህሊናዬ ሃዋርያቱ አንድ በአንድ ትዝ አሉኝ ብዋሽ ከእግዜር የሚሰወር የለም እውነቱን ብናገር እግዜርን ፈራሁት ምን ልመልስ?
asharaye.net
“ላለው ሁሉ ይሰጠዋል ይበዛለትማል……ከሌለው ግን ያው ያለውም እንኳን ይወሰድበታል” – Mistre Aderaw
http://asharaye.net/2015/04/09/ላለው-ሁሉ-ይሰጠዋል-ይበዛለትማልከ
ላለው ሁሉ ይሰጠዋል ይበዛለትማልከሌለው ግን ያው ያለውም እንኳን ይወሰድበታል. April 9, 2015. ይህንን አባባል ደጋግሜ ብሰማውም ትርጉሙ እሰከ ቅርብ ጊዜ እምብዛም አይገባኝም ነበር Rhonda Byrne የተባለችው ጸሃፊ ግን አባባሉ በህይወቴ ውስጥ ትልቅ ቦታ እንዲኖረው አድርጋዋለች ይህች አውስትራሊያዊት ፀሃፊ አለም የሚያውቃት The Secret ወይንም ሚስጥሩ በተባለው ብሩህ ህይወትን ለመምራት የሚያስችል የህይወት ፍልስፍናን በያዘው ስራዋ ነው በ2012 ያሳተመችው The Magic በተሰኘው መፅሃፏ ደግሞ አንድ ቃል የህይወትን ትርጉም ምን ያህል እንደሚለውጥ ድንቅ በሆነ ሁኔታ ለማስረዳት ሞክራለች. እስቲ ምስጋና የሚለውን ቃል በዓረፍተ ነገሩ ጨምረን እንደገና እናንብበው. ህይወትም ከዚህ የተለየ ባህሪ የላትም ላደረገችልን ነገር ባመሰገንናት ቁጥር ያለ እርህራሄ ሌሎች ምኞታችንን ታሳካልናለች.
asharaye.net
አጅሬ ገለባ……. – Mistre Aderaw
http://asharaye.net/2015/05/11/አጅሬ-ገለባ
አጅሬ ገለባ……. May 11, 2015. ታላቁ የቻይና ሊቅ ላዎ ቱዝ ዘ ዳዎ በተባለው መጽሃፉ ላይ ምዕራፍ ስምንት እንዲህ በሚያምር ሁኔታ ቀርቧል. አለምን ሁሉ ዝቅ ብሎ እንደሚያገለግለው እንደ ውሃ ሁኑ ሲል ጸሃፊው ከፍ ለማለት ስትሞክሩ የሰውነት ተፈጥሯችሁን እንዳታጡ ማለቱ ነው እንደው ብናስተውለው እኮ ብዙ ነገሮች ከተራራ ወርደው ዝቅ ወዳለው ስፍራ ይወርዳሉ እንጂ ከፍ ወዳለው ነገር መቼ ይወጣሉና ዝቅ ብለን መኖር ብንለምድ ህይወት ልፋት አትሆንም ሁሉም ነገር ዝቅ ወዳለው ቦታ ያለልፋት ሰተት ብሎ ይወርዳል ይህ የተፈጥሮ ህግ ነውና. የጭንቀታችን ሁሉ መንስኤ እራሳችንን ከተፈጥሮ ህግ ማራቃችን ነው ከልጅነታችን እስከ አሁን በማወቅም ባለማወቅም ያካበትናቸው አስተሳሰቦች ከእውነተኛ ተፈጥሮዋችን ለያይተውናል የሰው ልጅ ኑሮ የከበደው ሰው ስለሆነ ሳይሆን ከእውነተኛ ማንነቱ ጋር እጅግ ሰለተራራቀ ነው.
asharaye.net
ዛሬ ደግሞ እስቲ እኔ ልውለድሽ – Mistre Aderaw
http://asharaye.net/2015/05/11/ዛሬ-ደግሞ-እስቲ-እኔ-ልውለድሽ
ዛሬ ደግሞ እስቲ እኔ ልውለድሽ. May 11, 2015. እንዴት አድርጌ እንደማርግዝዥ ባላውቅም ልወልድሽ አስቤያለው ስቃይሽ አልገባኝ ቢል መስዋትነትሽን ባልረዳው ውለታሽን መክፈል ቢያቅተኝ ጥልቅ የሆነው እናትነትሽን ለመመርመር ቢከብደኝ በተራዬ ልወልድሽ ወሰንኩኝ ምን ላድርግ ፍቅርሽን እኮ የሰው ህሊና ሊመረምረው ውለታሽን የሰው ልብ ሊሸከመው አይችልም እንኳን ሰው እኔ የስጋሽ ክፋይ አልተረዳሁትም…….እናም ልወልድሽ ወሰንኩኝ. አየሽ ምጥሽን መረዳት ቢሳነኝ ስቃይሽን ውለታሽን መስዋትነትሽን መመዘኑ ቢከብደኝ በተራዬ ልወልድሽ ተመኘው ከንቱነቴ ነው ይህን ያስመኘኝ……ባለእዳ መሆኔ ህሊናዬን ዘወትር ስለሚያሳምመው ፍቅርሽን በተግባርሽ ባየውም ጥልቀቱን መረዳት ግን አልተቻለኝም ረቂቅ ሆንሽብኝ እናትነት እንዴት እንዲህ ውስብስብ ሆነ? ዛሬ እንዲህ ኩርምት ብለሽ ሳይሽ ከፋኝ….ልጅነቴን ጠላሁት...ደግነቷን ሳ...
asharaye.net
መነቃቂያ – Mistre Aderaw
http://asharaye.net/መነቃቂያ-2
በዚህ ገጽ የደከሙ መንፈሶችን የጠወለጉ ህይወቶችን ተሰፋ የቆረጡ ልቦችን የሚያክሙ እና የሚያለመልሙ ፅሁፎች የሚቀርቡበት ነው ሰው እንዳስተሳሰቡ ይኖራልና ኑሮዋችን እንዳሰብነው ካልሆነ አስተሳሰባችንን መፈተሹ መልካም ነው ለዚህም ነው የማነቃቂያ ፅሁፎችን ለመፃፍ እና ለአንባቢያን ለማስተላለፍ የወደድኩት. ሃሳብ ሲገባዎ ጭንቀት ሲፈታተንዎ ወደዚህ አምድ ጎራ ይበሉ እና መንፈስዎች ያድሱ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ካሰብን በአስተሳሰብ ጠንካራ ትውልድ መጀመሪያ መፍጠር እንዳለብን መዘንጋት የለብንም በዚህ ገፅ የሚቀርቡ ሃሳቦች በሙሉ እራሳችንን እንድንመለከት እና እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ናቸው ህይወታችንን መለወጥ ከፈለግን በመጀመሪያ አስተሳሰባችንን መቀየር ይገባናል. ምርትዎን ለመላው አለም በነፃ ያስተዋውቁ. ሶስት እርምጃ ለመክሊት; Three feet from your goal.
SOCIAL ENGAGEMENT